ሰበር ዜና


Breaking news
የኢትዮጵያ መሬትን ለሱዳን የመስጠቱ ጉዳይ እየተጣደፈ ነው።ኢትዮጵያዊነት የሚፈተንበት ሰዓት ነው።
የሱዳኑ ፕሬዝዳንት አልበሽር በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ናቸው።ዛሬ ጋምቤላ የብሔር ብሄረሰብ ጭፈራ ላይ ተገኝተው ምሽቱን አዲስ አበባ ገብተው ከአቶ ኃይለማርያ ጋር በጋራ ጉዳይ ያወራሉ ይላል የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ።
በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት የኢትዮጵያን መሬት ለይምሰል ምክርቤቱም ሳያቀርብ ከጎንደር እስከ ወለጋ ያለውን መሬት እና ወንዞች ጨምሮ ለሱዳን ለመስጠት መስማማቱ ሲገለፅ ቆይቷል።