ፍቅር እና ፅናት

Andargachew tsigie after his abdactionፍቅር እና ፅናት
የተራራቁትን አቀራረብካቸው፣
የተጠፋፉትን አገናኘሀቸው፣
የተለያዩትን አንድ አደረግሀቸው፣
ጥላቻን አጥፍተህ በፍቅር ዋጀሀቸው፡፡
የምስራቅ ኮከብ ነህ ከሩቅ የምትታይ፣
ታሪክህ ይነገር ይውጣ በአደባባይ፡፡
አንዳርጋቸው ሲሉህ ገና በልጅነት፣
ታይቷቸው ነበረ ይህ አንደሚከሰት?
የብርሀን ፀዳል የነፃነት ዓርማ፣
ታሪክህ ይነገር ገድልህ ይሰማ፡፡
አንተ ሰማእት ነህ ከሰማእት በላይ
ዓላማህ ከሩቁ ለሁሉም የሚታይ፡፡
እንኳን ለደቂቃ ለወራት ቢያወሱ፣
መች በቂ ይሆናል አንተን ማስታወሱ፡፡
ህይወትክን ሰጥተህ ፍቅር ያለበስከን፣
ዘር ቀለምን ሳትለይ አርአያ የሆንከን፣
ቤዛችን ነህና ዘላለም ኑርልን፡፡
ለመርዘኞች ሴራ ፍቱን መድሀኒት ነው
የጠብን ግድግዳ በፍቅር የናደው
ቅኔ ምወድሱ ዝማሬው ለሱ ነው፡፡
ነፃነት ሳያውቁ ነፃ አውጪ ነን ብለው፣
ከህዝቡ ጫንቃ ላይ በግድ ተሰቅለው፣
ሴራ እየሸረቡ ጉድጉዋድ ሲምሱልን፣
ገድለው ሳይጨርሱን ማስወገድ አለብን፡፡
ወንጀለኞች ፈራጅ በሆኑባት ሀገር፣
ገዳዮች አሳሪ በሆኑባት ሀገር
ምን መፍትሄ አለና ከመሳሪያ በቀር፡፡
ፍትህን ተጠምታ የቃተተች ነፍስህ፣
ቤት ልጆች ሳትል በረሃ ብትክልህ፣
ለነፍሰ-በላዎች ተላልፈህ ተሰጠህ፡፡
ደርቆ የነበረው የተስፋችን መንፈስ፣
የትግል ወኔያችን በቃልህ ሲታደስ፣
ህመምህ ተሰማን አጥንታችን ድረስ፡፡
እጅ እግርህን አስረው ለግዞትቢያወርዱት
የታነጸበትን መሰረት ላይንዱት
የትግሉን ነበልባል ፍሙን ላያጠፉት
አመድ ሁኗል ብለው ያዳፈኑት እሳት
ይኸው ተቀጣጥሏ ተዛምቷል በስፋት
የነፃነት መንፈስ ማሰር የማይችሉት፡፡
የዛሬው አበባ ነገ ፍሬ አፍርቶ፣
የገደለሽ ሳይሆን የሞተልሽ በልቶ፣
ባንተ ይታየናል ህልማችን ተሳክቶ፡፡
እኩልነት ሰፍኖ የዘር ሾተል ነቅለን፣
ብርሀኑን ልናይ ጨለማውን ገፈን፣
በአንድነት መጥተናል ጥሪህን አድምጠን፡፡
ዛሬ ብትርቀንም ባትኖር ከጎናችን፣
ሁሌም ካንተ ጋር ነው መላ ስሜታችን፡፡
የነፃነት ታጋይ ዘመን የማይሽርህ፣
ፍቅርን ከፅናት አሟልቶ የሰጠህ፣
የኛ ማርቲንሉተር የኛ ምንዴላ ነህ፡፡
መታሰሰቢያነቱ መላ ህይወቱን በኢትዮጵያ ፍትህ፤ነፃነት እና እኩልነት እንዲሰፍን አሳልፎ ለሰጠው እና ዛሬ በዘረኛ አረመኔዎች እጅ ወድቆ ሲቃይ እና መከራ እየደረሰበት ላለው የነፃነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፡፡
ኦገስት30.2014